የሱዳን፣ የኤርትራና የግብጽ ዜግነት ባላቸው ራሻይዳዎች ታፍነው ወደ ሲና በረሃ የተወሰዱት ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ ካይሮ መግባታቸው ታወቀ። ወ/ሮ ትዕግስት ቅዳሜ ረፋዱ ላይ ካይሮ የገቡት አጋቾቹ እንዲሰጣቸው ከጠየቁት 25 ሺህ ዶላር በድርድር 15 ሺህ ዶላር ተከፍሏቸው ነው። ዜናውን በሰሙ ማግስት “የወ/ሮ ትግስት የርዳታ እጆች” በማለት ተሰባስበው የነፍስ አድን ዘመቻውን ከጀመሩት መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ሰብለ ደምሴ [...]
↧