ቢሄዱት… ቢሄዱት… ቢሄዱት… ቢሄዱት… አያልቅ ሽቅቦሹ፥ አይቆም ቆልቁሎሹ መንገድ እየሄዱ መንገድ እየበሉ መንገዱ እየጠጡ አያልቅም ቢሄዱት፥ አያልቅም ቢጠግቡት፤ አወይ አማሪካን… አወይ የሰው አገር የበላን ያላየ፥ የዋጠን ያልሰማ አወይ አማሪካን፥ ሰው በላብ ያደማ፤ ቢሄዱት ቢሄዱት፥ እረፍትን ማን አውቆት እዚማ ከሆኑ… እንቅልፍ ለምኔን፥ ለብሶ ነዪ መኛት፤ አወይ አማሪካን፥ አገረ ማራቶን አገረ እሩጫ ለማምለጥ መፏደድ፥ ቢል ከሚሉ ጡጫ [...]
↧