በፌዴራል ስም የተሸፈኑ ህውሃት/ኢህአዴጎች እና በአቶ መለስ ራዕይ የተጠመቁ የክልል ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ የዘር ማጥራት (Ethnic Cleansing) ወንጀል ስለመፈጸማቸው መዘገብ ከጀመረ ውሎ አድሯል። ይኽ ዜና በኢትዮጵያ ወዳጆች ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ዜጎች ዘንድ ስጋት ፈጥሯል። ኢትዮጵያ እንድትበተን የሚፈልጉ ግን አፍና እጃቸውን አስተባብረው ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከመንገዳቸው ላይ ተወግዳ ህልማቸው ወደሆኑት የቃል-ኪዳን አገሮቻቸው (Promised-land) ለመድረስ የጀመሩትን ጉዞ ፍጥነት [...]
↧