ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳቹህ እጽፍላቹህ ዘንድ ግድ ሆነብኝ ይሁ. 1፤3 በዚህ ጽሑፍ ላይ ጥንታዊቷና ሀገር በቀሏ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ ከምእመናኗ ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ ማሽቆልቆል መንስኤውንና ተጓዳኝ ነገሮችን እናያለን፡፡ ይሄንን እንድናይ ግድ የሚልበትም ምክንያት ይህ አደጋ ኢትዮጵያዊ የሆነውን ማንነትና እሴት ለማጥፋት በተለያየ መንገድ ሲጥሩ የኖሩ ባዕዳን ጥረታቸው ሠምሮላቸው አሁን ላይ ኢትዮጵያዊነት [...]
↧