ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ያህል የዓለም ባንክ በተለይ ከሲቪል ማኅበረሰቦች ጋር ሲያካሂድ የነበረው ስብሰባ “በመፈንቅለ ዓለም ባንክ” ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያን በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ መድረኮች በመወከል ድምጻቸውን የሚያሰሙት ኦባንግ “በመፈንቅሉ” ከተሳተፉት የዓለም ሲቪል ማኅበረሰቦች መካከል ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ነበሩ፡፡ የዓለም ባንክ ስለሚሰጠው ብድርና ዕርዳታ በተመለከተ ሊያካሂድ ያሰበው የፖሊሲ ለውጥ ሰነድ አፈትልኮ ከወጣ ጀምሮ በርካታ በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሟገቱ [...]
↧