Quantcast
Channel: Goolgule
Viewing all articles
Browse latest Browse all 3174

ናፍቆት (በኑሬ)

$
0
0
ስጋዬ ሲበላኝ በጥርሴ ነከስኩት፤ ቆዳዬ ሲበላኝ በጥፍሬ ፎከትኩት፤ እፎይ አስታገስኩት፤ ፀጥ ረጭ አረ’ኩት። የውስጥ አጥንቴ ግን ሲበላኝ ነዝንዞ፣ ሲነክሰኝ ጠዝጥዞ፣ ምንም አላረ’ኩት፤ ምንም አላከኩት፤ ላልችል ችየ ቻልኩት። አልፎክተው ነገር ቆዳዬን መንቅሬ፣ አላኝከው ነገር ስጋዬን ሰርስሬ፣ ይሔው እስከዛሬ፣ አጥንቴ እየበላኝ፣ አለሁልሽ ፍቅሬ። ኑረዲን ዒሳ (ዒሻራ) 14/02/1995 ዓ.ም

Viewing all articles
Browse latest Browse all 3174

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>