አቶ ኑሮ ውድነህ አምና የአዲስ ዘመን በዓልን አስመልክቶ ቤተሰባቸውን ለማስደሰት በማሰብ ያላቸውን ገንዘብ አሰባስበው ገበያ ይሄዱና የበግ ዋጋ ይጠይቃሉ። ሆኖም የበጎቹን ዋጋ ሲሰሙ የሚሮጡት የርቀት መጠን በሜትር እየተነገራቸው እንጂ መሸጫ ዋጋቸው አልመስል እስኪላቸው ድረስ አስደንጋጭ ይሆንባቸዋል። አውጥተው አውርደው ግን ለቤተሰባቸው መጠነኛም ብትሆን በግ በመግዛት ሃሳባቸው ላይ ፀንተው ረከስ ባለ ዋጋ እጅግ ቀጫጫ የሆነች ግልገል በግ [...]
↧