ያለሁት ካናዳ፤ ቶሮንቶ ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ትላንት ማታ አንዱ የኢትዮጵያ ምግብና ዳንኪራ ቤት ለማምሸት ከዘመድ እና ሰሞኑን ከተዋውቅኳቸው ጥቂት ሰዎች ጋር ሄድኩ፡፡ ቤቱ በአንድ ሰሞን በአንድ ዜማ እጅግ ታዋቂ ሆኖ በነበረ ወጣት ድምፃዊ የሚተዳደር ነው፡፡ ስገባ ወጣቱን ድምፃዊ አየሁት፡፡ እንግዶቹን ዞር ዞር እያለ ሰላም ይላል፡፡ ከማውቀው ወፍሯል፡፡ ዘመናዊም ባህላዊም ዘፈን በዲጄ ሲለቀቀቅ ጠባቧ [...]
↧