ጠመዝማዛ ባላዎች ላይ የቆመው ክፍል በደደሆ ዛፍ ቅጠል የተሠራ ጣሪያ አለው፡፡ ክፍሉ ውስጥ ከ20 የማይበልጡ ትንንሽ ድንጋዮች ላይ ኩርምት ኩርምት ብለው የተቀመጡ ተማሪዎች ይታያሉ፡፡ ደብተሮቻቸውን በየጉልበታቸው ላይ አድርገው ከፊት ለፊታቸው ያለውን መምህር ያዳምጣሉ፡፡ ከመሬት ብዙም የማይርቀው የክፍሉ ጣሪያ መምህሩን ጐንበስ ብሎ እንዲያስተምር ግድ ብሎታል፡፡ መምህሩ ለማለቅ በተቃረበ ነጭ ጠመኔ ያረጀ ሰሌዳ ላይ ቁጥሮች እየጻፈ ድምፁን [...]
↧