ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድናችን በደቡብ አፍሪካ ያስመዘገበው ውጤት እስካሁን የብዙዎች መነጋገሪያ ዋና ሃሳብ ሆኗል፡፡ በተለይ ከእግር ኳሱ ጋር የታየው ወዳጅነት፤ አብሮነትና ተደጋጋፊነት ፖለቲከኞቻችንን “እንዴት ነገሩ፤ ካልሆነ … ብትሞክሩትስ?” የሚያስብል ሆኗል ቢባል የተጋነነ አይሆንም፡፡ ለዛሬ የግጥም ጨዋታ ይህንኑ መንፈስ የሚያንጸባርቅ ወቅታዊ ጨዋታ እንደሚሆን በማሰብ ከድንቅዬ ገጣሚዎቻችን መካከል ብሌን ከበደ በፌስቡክ ላይ የለቀቀችውን ከታላቅ ምስጋና ጋር እነሆ [...]
↧