የእግር ኳስ ጨዋታ ለኢትዮጵያዊያን ከረጅም ርቀት ሩጫ ውድደር ጋር ከፍተኛ ቦታ የያዘ ነው። በእድሜያችን ገፋ ላልነው፤ የነመንግሥቱ ወርቁ የኳስ ጥበብ፤ የኢታሎና ሊቻኖ . . . ኧረ ስንቱን በትዝታ ዓለም መጎብኘት ይቻላል። ብቻ ለሁሉም ያንን እንዳስታውስ ያደረገኝ፤ በዛሬው ዕለት ከቤቴ ተቀምጨ ያየሁት የኢትዮጵያ ቡድንና የዛምቢያ ቡድን ጨዋታ ነው። ቡድናችንን በሀገራችን ካለው ዘረኛ አገዛዝ ነፃ አውጥቶ ለብቻው [...]
↧