በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡ ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት [...]
↧