በ1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫና ምርጫውን ተከትሎ ተከስቶ በነበረው የፖለቲካ ውዝግብ አካል የነበሩት የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ አና ጐሜዝ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም. ተካሂዶ የነበረውን ምርጫ በአውሮፓ ኅብረት ተወክለው ምርጫውን በዋና ታዛቢነት የመሩትና የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጐሜዝ፣ ምርጫውን አስመልክቶ ባወጡት ሪፖርት ኢሕአዴግ ከሚመራው መንግሥት ጋር ጥልቅ የሆነ [...]
↧