አዎ፤ የኔም እምባ ፈሷል እምነቴ ደፍርሷል ሰበዕናየ አንሷል ምክንያት ፍለጋ – መፍትሄ ፍለጋ ቀኑ እስከሚጨልም – ሌሊቱ እስቲነጋ ብቆርጥ ብቀጥል – ባነሳ ብጥለው ዘላለም ሆነብኝ – ማለቂያ የሌለው ሕመምሽ አሞኛል ድካምሽ ደክሞኛል እምባሽን ለመጥረግ – አቅም በማጣቴ ሕሊናየ ቆስሏል – ተቃጥሏል አንጀቴ እና….ጠንክሪ እህት ዓለም ይሄም ቀን ይረሳል – እንደማያልፍ የለም
↧