“ሐጫሉ የሚሰራቸውን አዳዲስ ሙዚቃዎች አንሰማ ይሆናል። ግን ዘላለማዊ ነው። ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገሩ፤ ትውልድን ለትግል የሚያነሳሱ፤ ሐጫሉ የቆመለትን ዓላማ ከግብ የሚያደርሱ ሥራዎችን ሰርቶ አልፏል። መሞቱን እያወቀ፤ መስዋዕትነት እንደሚከፍል እያወቀ የኖረ እና የተሰዋ ሰው ነው። ሙዚቃዎቹን ለዘልዓለም እንሰማቸዋለን” አቶ በፍቃዱ ሞረዳ በልጅነቱ የሙዚቃ ተሰጥዖውን ከሞረደባቸው መካከል የዳዊት መኮንን ሥራዎች ቀዳሚ እንደሆኑ ይናገር ነበር። ጊታር፣ ኪቦርድ እና ክራር […]
↧