መለስ ህይወታቸው እንዳለፈ ከተሰጡት አስተያየቶችና ትንቢቶች መካከል ቀዳሚው የመለስ ሞት ለህወሃት ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ፈንጂ መሆኑ ነበር። በዚሁ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በስልጣን ላይ ያሉ የኢህአዴግ ዲፕሎማት “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህ እንደሚከሰት ቁልጭ አድርገው ተናግረው ነበር። መለስ አፍነው የያዟቸው የፖለቲካ ችግሮች ጊዜያቸውን እየጠበቁ የሚፈነዱና በመጨረሻም ፓርቲውን እንደሚፈረካክሰው የተገለጸው በየደረጃ የሚፈነዱት ችግሮች [...]
↧