ዐባይ ቢሻው ይጉረፍ በጣና ላይ ነግሶ አሎሃ ይደፍርስ ተከዜም ደም ለብሶ ማሂንም አቋሽም ጓንግም በሙላቱ መሻገሪያ ይንሳ እስኪያልፍ ክረምቱ ይፎክር ያቅራራ ይኩራ በጉልበቱ ድሮም እንዳይፀዳ በጎርፍ ውኃ ታጥቦ የጀግና ሰው ሞቱ ያውቃሉ እናውቃለን ዛሬም እንደ ጥንቱ ደም በደም ይፀዳል ደም ነው ሥርየቱ። ለጀግና ዕምባ አይረጩም ፀጉርም አይላጩም ዋይታና ለቅሶ ሙሾ አይደረድሩም ወይም ፊት አይነጩም እንደ […]
↧