በቱኑሲያ፣ በግብጽ፣ በየመን፣ በሊቢያና በባህሬን የተከሰተውን የአረብ ጸደይ ተከትሎ፤ ሶሪያውያን ለአመጽ ሲነሱ፤ ሀገራቸው የተመሰቃቀለ ታሪክና ኅብረተሰባዊ ትስስር ስለነበራት፤ ትግላቸው መራራ፣ የከፋና ጊዜ የሚወስድ መሆኑን በመገንዘብ፤ ቀሰስ ብለው ነበር የተነሱት። እውነትም እንዳሰቡት ሆነና፤ አሁንም ትግላቸው እያዘገመ፤ የሚከፍሉት መስዋዕት እየበዛ፤ የድል ቀኑም እየረዘመ ነው። ለአራት አስርታት ዓመታት ከአባትየው ሃፌዝ አል-አሳድ ጀምሮ፤ አምባገነናዊ አገዛዝ ያዘነበባቸው አረመኔ ግፍ ስላንገሸገሻቸው፤ […]
↧