ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለጓደኞቻቸው በሙሉ፤ ሰላምታዬን አቀርብላችኋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር አገር ነች፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነው፤ ክርስቲያኑም፣ እስላሙም፣ አረመኔውም የእግዚአብሔር ነው፤ እንደየእምነቱ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚኖር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጊዜ የተለየ ነው፤ ትእግስቱን ስለሚያረዝመው የተረሳ ያስመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግፍን አይረሳም፤ እግዚአብሔር ሁሌም ለአቅመ-ቢሶች ጉልበት የሚሆንበት መንገድ አለው፤ ግፍ በእግዚአብሔር በር ላይ እንደተጣለ ግም ቆሻሻ ነው፤ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ይጠርገዋል፤ ወይም […]
↧