ዱሮ እረኞች በነበርንበት ጊዜ ታላላቆቻችን ይሰበሰቡና እኛን ታናናሾቻቸውንን ጠርተው እርስ በርሳችን ትግል እንድንጋጠምና አሸናፊውም ከዛ ቀን ጀምሮ ላሸናፊው አለቃና አዛዥ እንዲሆን ያደርጉት ነበር፤ ውድድሩ አንዳንድ ጊዜ ከዚህም የከፋ መልክ ነበረው። ተወዳዳሪዎች መደባደሚያ ዥልጥ (የዛፍ ግንጣይ ማለት ነው) ይሰጣቸውና ጎረምሶቹ በተሰበሰቡበት እንዲደባደቡ ይደረጋል። ተጋጣሚዎቹም በፍርሃትና ባልሸነፍም እልህ ከአይንና ጥርስ በቀር አካል ሳይመርጡ ይናረታሉ። ጎረምሶቹ (ባካባቢው አጠራር […]
↧