ሰማያዊ ፓርቲ “ኢህአዴግ” የሚል ውህድ ፓርቲ እንዳለ ተደርጎ በህግ ጥሰት በስሙ የተመዘገቡ ሁሉም ዕጩዎች እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድን ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ የካቲት 30/2007 ዓ.ም ለምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምግዝባ አዋጅ ‹‹’ግንባር’ ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተናጠል ህጋዊ ህልውናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጋራ የሆነ ስያሜ፣ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ኖሯቸው ለመንቀሳቀስ ሲወስኑ [...]
↧