1.መቅድም ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው። ጳውሎስ ኞኞ ኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በሚለው መጽሃፉ እኛ ስለራሳችን ስንጽፍ እናጋንናለን ስለዚህ የውጭ አገር ምእራባውያን የመሰከሩልንን [...]
↧