የትግሬ ወያኔ በኃሣብ፣ በዕቅድ እና በተግባር ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነ ድርጅት መሆኑን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ሠሞኑንም ከመገናኛ ብዙሃን የሚደመጠው «የትግራይ ድንበር አል-ውሃ ድረስ ነው» የሚለው ወሬ የዚሁ የሚጠበቀው የትግሬ-ወያኔ ተከታይ እርምጃ እንደሆነ አያጠያይቅም። ኢትዮጵያን የማፈራረሱ የንድፈ-ኃሣብ መሠረት የተጣለው በተለያዩ የውጭ ኃይሎች እንደሆነ ይታወቃል። ከእነዚህ መካከል ሮማን ፕሮቻዝካ የተባለው የኦስትርያ-ሐንጋሪ መሥፍን (Baron [...]
↧