Quantcast
Channel: Goolgule
Viewing all 3165 articles
Browse latest View live

100% ደፋኝ “ጎበዞች”

$
0
0
በ1994ዓም የኢራቁ ፕሬዚዳንት ሳዳም ሁሴን “በምርጫ” 100% ደፍነው ነበር፡፡ ያለፈው ዓመት ደግሞ የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ-ኧን ያለአንዳች ተቀናቃኝ ባደረጉት “ከፍተኛ ትንቅንቅ” በነበረበት የምርጫ ውድድር ብቻቸውን ተወዳድረው በመጨረሻው ላይ ትንፋሻቸውን ይዘው 100% ለመድፈን በቅተዋል፡፡ ሳዳም 100 ከደፈኑ በኋላ ብዙም አልቆዩም፡፡ በሌላ በኩል የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ ታላቁ ባለራዕይ መሪ ኪም ጆንግ ኢል ከልጃቸው ኪም ጆንግ-ኧን በ0.1% በመበለጥ […]

በቅድሚያ ከራሳችን እንታርቅ

$
0
0
አቶ ፈቃደ ሸዋቀና የስደትን ነገር መነሻ አድርገው ስለ ብሔራዊ እርቅ የሰነዘሩት ሀሳብ ካለፈው የባሰ ጨለማ የሆነው የሀገራችን መጻኢ እድል አሳስቦ አስጨንቆአቸው ያቀረቡት በጎ ሀሳብ እንደመሆኑ አንብበን የምንተወው ወይንም ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ብለን ልናናንቀው የሚገባ አይደለም፡፡ ርሳቸውም አንዳሉት ሁሉም የየበኩሉን ይበጃል የሚለውን ሀሳብ በመሰንዘር በመተላለቅ ሳይሆን በመታረቅ የምናተርፈበትንና ሀገራችንንም አድነን ለመጪው ትውልድ ልጆቿ በሰላምና በፍቅር የሚኖሩባት […]

የትግሬ-ወያኔ አቅጣጫ ከ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በኋላ

$
0
0
የትግሬ-ወያኔ አመራር በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ ዐማራን ፈጽሞ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይወስደው ዳግም አረጋገጠ! «ትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ዐማራው ስለሆነ፣» እያንዳንዱ ትግሬ ዐማራን በማጥፋት እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን፣ የወያኔ የአገር-ውስጥ እና የውጭ የስለላ ቡድኖች ከፍተኛ አመራሮች በጥናቶቻቸው እንዳሣዩ የታመኑ የሞረሽ-ወገኔ ምንጮቻችን አረጋገጡ። የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት፣ አጥኚዎቹ ከሕወሓት ፖሊት ቢሮ በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት የትግሬ-ወያኔን ዘረኛ […]

“የአማራ ክልል ዳኞች አቤቱታ”

$
0
0
ከአዘጋጆቹ፡- ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፌስቡክ ወዳጃችን “የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን” በማለት በውስጥ መስመራችን የላኩልንን ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡ ጋዜጠኝነት “ወንጀል” በሆነባት ኢህአዴግ በሚገዛት አገራችን በስም የተጠቀሱትን ሹመኛ ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማረጋገጥ አንችልም፡፡ ሆኖም ግን መረጃው ስህተት ነው የሚል የኢህአዴግ አካል ምላሽ ከሰጠን ለሕዝብ እናቀርባለን፡፡ “የአማራ ክልል ዳኞችን ድምፅ አስተጋቡልን”!!!!! ደመወዝና ጥቅማጥቅም ስላነሰን ከእነ ልጆቻችን ተራብን፣ ተጠማን፣ […]

“ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ይጋቡ” ጠቅላይ ፍርድቤት

$
0
0
* “ፍቅር ፍቅር ነው” ኦባማ ወንድ ከወንድ፤ ሴትም ከሴት ጋር ጋብቻ መፈጸም ይችላሉ፤ ለእነርሱ የጋብቻ ሠርቲፊኬት መከልከል ሕገመንግሥቱን ይጥሳል በማለት የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መጋባት እንደሚችሉ ወሰነ፡፡ ለጋብቻ ቅድስናና ክቡርነት የሚከራከሩ “የእግዚአብሔርን ሕግ ምድራዊ ፍርድ ቤት ይህን መለወጥ አይችልም” በማለት ውሳኔውን አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡ በምንም መልኩ ይገለጽ ፍቅር ፍቅር ነው በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ […]

የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሄት

$
0
0
“ትግሌን አደራ” ነፃነቱን የተቀማ ሕዝብ ለድል የሚያበቃው ጠንካራ ድርጅት ይፈልጋል ምርጫና የሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ ምርጫ 2007 ሂደቱም ሆነ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብትና ደህንነት የሚጠብቅ መንግሥት የላትም በመሳሰሉና ሌሎችም ርዕሶች መጽሄቱ ታትሞ ወጥቶዋል – ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ከገዥው ወገን የምንለይበት

$
0
0
እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለትግሬዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦሮሞዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአማራዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሶማሌዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአፋሮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦጋዴኖች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአኙዋኮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሲዳማዎች ጥብቅና […]

አለም አቀፍ ድጋፍ የተቸረው “ልማታዊ” አንባገነናዊነት በኢትዮጵያ

$
0
0
“የአፍሪቃ ድሃ ባይጠግብም እንኳ ቀምሶ ካደረ ይበቃዋል” አይነት ንቀት የተሞላው የምዕራቡ አለም ምልከታ ከመቼውም ጊዜ በከፋ መልኩ አፍጦና አግጦ እየታየ ነው፡፡ በርሃባችንና በእርስ በእርስ መናቆራችን ለዘመናት ሲነግዱበትም ሲማረሩበትም ቆይተዋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የመጫወቻው ካርድ ተቀይሮ ለአፍሪቃ አንባገነኖች አንድ ቃል ተለጥፎላቸው ካሳላፍነው ታሪክ ምናልባትም በከፋ መልኩ ጉዟችንን ቀጥለናል፤ የኋሊት ይሁን ወደፊት እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን የምዕራቡ አለም […]

…አልሞት አለኝ

$
0
0
በስራው ላይ ልፈላሰፍ ቅኔ ልቀኝ ግጥም ልጽፍ ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ የማደንቀው ሰው ነበረኝ ሳይሞትማ ሳይቀበር ስሙን ማንሳት እሱን ማክበር መስሎ ታይቶኝ ልምድን መስበር የማደንቀው ሰው እያለኝ ልጽፍለት ተቸገርኩኝ አቤት! ዕውቀት አይ! ቁመና ብልህ ደፋር ቆራጥ ጀግና ሀይማኖቱን አጠንካሪ ደግ ለጋስ ሰው አክባሪ ብዬ ልለው ቸኩያለሁ አልሞት ብሎኝ ታሞ እያየሁ ዛሬ ቢያጣ ዛሬ ቢርበው በቁም ሆኖ […]

የሰላም ትግሉ በኢትዮጵያ (ክፍል ፪)

$
0
0
በክፍል አንድ፤ የሰላማዊ ትግሉ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ምን እንደሆነ ገልጫለሁ። በዚሁ ላይ፤ የሰላማዊ ትግሉ ከተወዳዳሪ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ልዩነት አሳይቻለሁ። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሰላማዊ ትግሉ የሚካሄደው በአንድ የሕዝባዊ ንቅናቄ ድርጅት ሥር ብቻ መሆኑንና፤ አማራጭና ተለዋጭ እንደሌለው አስምሬበታለሁ። በሂደቱ መሰባሰቢያ የሆኑትን ሀገር አቀፍ የትግል ዕሴቶች አስቀምጫለሁ። በዚህ ክፍል ሁለት ደግሞ፤ ስለተሳሳተው የሰላማዊ ትግሉ ግንዛቤያችን አስረዳለሁ። ባጠቃላይ፤ […]

የነፃነት መውጫው መንገድ፣ ታጋዩ፣ ሕዝቡን ጠንካራ ምሽጉ ማድረግ ሲችል ነው

$
0
0
የአንድ ለነፃነት የሚታገል ኃይል የመጀመሪያ ተግባሩ፣ ጠንካራ ምሽግ መገንባት ነው። ምሽግ ሲባልም መሬትን ጎርዶ ራስን መቅበር፣ ወይም ደግሞ በኮንክሪት መከታ እና ጠለላ ገንብቶ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወነጨፉ አውዳሚ የጦር መሣሪያ አረሮችን መከላከል አይደለም። ጠንካራ ምሽግ ሲባል፣ ታጋዩ ኃይል ነፃ አወጣዋለሁ የሚለውን ሕዝብ፣ ዓላማውን አሳውቆ፣ አሳምኖ እና አደራጅቶ የታጋዩ ኃይል የቀለብ፣ የመረጃ እና የሰው ኃይል ምንጭ ማድረግ […]

የ“ኢህኣዴግ” ግምገማና ፍሬው

$
0
0
በድርጅት ከዚያም ከፍ ብሎ በመንግስት ደረጃና በሃገር ደረጃ ግምገማ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ሁሉ ያምናል። የኣንድ ድርጅት ብቃትም በግምገማው ችሎታና ጥራት ሊለካ ይችላል።የኣንድ ሃገር የፖለቲካ መረጋጋት በፖለቲካ ለሂቆቹ የጠራ የሃገር የምናብ ስእልና ብስለት ሊለካም ይችላል። የፖለቲካ ቤቶች ሲኮለኮሉ፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ ከፍ ያለ ግምገማን ይጠይቃል። ሃገሪቱ ያለፈችበትን የህይወት ጎዳና፣ የገጠማትን ችግር መንስዔና ውጤቶች በሰፊው መገምገም ለሚመሰረቱ […]

“የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” !

$
0
0
ሰሞኑን ኦባማ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው በሚል፤ ከባህር ማዶ ጫጫታ፤ ከወደ አገር ቤት ደግሞ የጆሮ ብራና የሚጠልዝ ከበሮ ድለቃው ተጧጡፏል:: ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

በኤርትራ ላይ ምርመራው እንዲቀጥል ተወሰነ

$
0
0
በኤርትራ ላይ የሚካሄደው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ የሚጠረጠረውን በሰብዕና የሚፈፀም ወንጀል እንዲያካትት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ትናንት ወስኗል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እንዲመረምር የተቋቋመው ልዩ አጣሪ ኮሚሽን ሥራውን በአንድ ዓመት እንዲያራዝም የተስማማው አርባ ሰባት አባላት ያሉት የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ክትትል አካል ነው፡፡ ምርመራው ሙሉ ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ እንዲካሄድ […]

“የሳሙኤል ግድያ ለታጋዮችም ለገዳዮችም ትልቅ ትምህርት ነው!”

$
0
0
ስለ ሳሙኤል ግድያ ብዙ ነገር ተብሏል፡፡ ብዙዎች ቁጭታቸውን ገልፀዋል፡፡ ለእኔ ከሳሙኤል አወቀ ግድያ ምን እንማራለን? የሚለው ነው ትልቁ ቁም ነገር፡፡ ሳሙኤል በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ንግግር ተናግረው የተገደሉ ሰዎች ጋር የሚመደብ ሰው ነው፡፡ የሳሙኤል ትውልድ አካል በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፡፡ እንደገሚገሉት እያወቀ፣ ነገር ግን ያ ሞቱ ከንቱ እንዳይሆን አስፈላጊውን መረጃ አስቀምጦልናል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ መንፈሳዊ አባት ማለት ምን […]

ይድረስ ለገራፊዎቻችን –እኛ የፀናነው እናንተንም ነፃ ለማውጣት ነው!

$
0
0
“በምርመራው ወቅት የነበረው ድብደባ እና ክብረ ነክ ስድብ ወደ ምድር የመጣሁበትን ቀን እንድረግም አደረጉኝ፡፡ በተለይ ከአሁን በኋላ ልጅ መውለድ እንደማልችል እየዛቱ የውስጥ እግሬን ክፉኛ ገረፉኝ፡፡ . . . እኔም ልብሴን እንደማላወልቅ ነገርኳቸው፡፡ በዚህም ከአሁን ቀደሙ ለየት ያለ ከባድ ድብደባ አስተናገድኩ፡፡ ድብደባው ከአቅሜ በላይ ሲሆን ግን ከውስጥ ሱሪዬ ውጭ ያለውን ልብሴን ለማውለቅ ተገደድኩ፡፡ የውስጥ ሱሪዬንም እንዳወልቅ […]

ያልተፈቱት “አሸባሪዎች”

$
0
0
1 – ተመስገን ደሳለኝ 2- እስክንድር ነጋ 3- ናትናኤል መኮንን 4- አንዳለም አራጌ 5- ውብሽት ታዬ 6- አበበ ቀስቶ 7- ሃብታሙ አያሌው 8- ድልንኤል ሺበሺ 9- አብርሃ ደስታ 10- የሽዋስ አሰፋ 11- ዘላለም ወርቅአገኘሁ 12- አቤል ዋበላ 13- ናትናኤል ፈለቀ 14- በፍቃዱ ሃይሉ 15- አጥናፍ ብርሃኔ 16- ፍቅረማርያም አስማማው 17- እየሩሳሌም ተስፋው 18- ብርሃኑ ተክለያሬድ […]

ሃዲያ ሞሃመድ! ያልተዘመረላት ጀግና

$
0
0
ያልተዘመረላት፣ ያልተነገረላት ጀግና ኢትዮጵያዊት ሴት ናት። እንደሌሎች “እኔ ምን አገባኝ? አርፌ ልቀመጥ” ብላ፣ ባርነትንና ዉርደትን አሜን ብላ ተቀብላ፣ ሕሊናዋን ሸጣ፣ የገዢው ፓርቲ አዉደልዳይ ሆዳም ካድሬና አገልጋይ ሆና፣ በዘረኝንትና በጠባብነት በሽታ ተለክፋ መኖር ትችል ነበር። ግን አላደረገችውም። ከደቡብ ክልል ከወላይታ ሶዶ ናት። የወያኔ ቡችላው ሃይለማሪያም ደሳለኝ መጣሁበት ካለው። እንደ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሌሎች አሽከር አልሆነችም። እንደ ኃይለማሪያም […]

የግፍ ሠንደቅ ወረደ!

$
0
0
በአሜሪካ የደቡብ ካሮላይና ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ የሸንጎ ሕንጻ ላይ ከ50 በላይ ሲውለበለብ የነበረው ሠንደቅ አርብ ወረደ፡፡ “ውሸት ለዘላለም መቆየት አይችልም፤ የዘረኝነት ምልክት እና ዘረኝነት መፍረስ ይገባቸዋል” በማለት የሠንደቁን መውረድ የደገፉ ተናገሩ፡፡ በእንግሊዝኛው አጠራር “የኮንፌዴሬት” ሠንደቅ የሚባለው በአሜሪካ የእርስበርስ ጦርነት ወቅት ከኅብረቱ ለመለየት የፈለጉ ግዛቶች የራሳቸውን ፕሬዚዳንት መርጠው ከኅብረቱ ደጋፊዎችና አብርሃም ሊንከን ጋር ጦር በገጠሙበት […]

ክብሩ የተነካው የክብር ዶክትሬት

$
0
0
እንደብዙዎቹ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ዩኒቨርሲቲው በየጊዜው የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር እንዲከፍቱ ለመረጣቸው ታላላቅ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ይሰጣል፡፡ እ.ኤ.አ. 2009 ላይ ግን የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን በንግግር ለከፈቱት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የክብር ዶክትሬት ላለመስጠት መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፕሬዚዳንቱ ልምድና የሥራ ውጤት ለክብር ዶክትሬት ጣሪያ አልደረሰም የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ጉዳዩ በተወሰነ መልኩ ውዝግብ አስነስቶ […]
Viewing all 3165 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>