በተለያዩ ሀገሮች የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ያለፉባቸውን ጥምዝምዞች፣ የገጠማቸውን ደጋፊና አደናቃፊ ሂደቶች መመርመር ባንድ ሀገር ውስጥ ለሚካሄደው ትግል ታላቅ ጠቀሜታ አለው። በዚህ አንጻር በ2011 የአረብ ስፕሪንግ ካምባገነናዊ ስርአት ወደ ዴሞክርሲ ልትሸጋገር ነው ተብላ ተስፋ የተጣለባት የመን፣ እነሆ ዛሬ በእርስ በርስ ጦርነት ተናውጣ እንኳንስ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ልትሸጋገር ከራሷም አልፋ አካባቢውን ለማመስ የቻለ ሁኔታ ውስጥ ገብታለች። ይህ እንዴት […]
↧
በየመን የሚታየው ምስቅልቅል እየሰፋ ስለመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጥረት ምን ያስተምረናል?
↧
እረኛ የሌለው ከብት እና መሪ የሌለው ሕዝብ አንድ ናቸው
ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ የደረሱባቸው ከፍተኛ ሰቆቃዎች አሉ። አምና በሣዑዲ ዓረቢያ፣ ባለፉት ሁለት ወራት ደግሞ በየመን በሚኖሩ የዕለት እንጀራ ፈላጊ በሆኑ በመቶ-ሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተጸፈመባቸው ግፍ የተሞላበት ግድያ እና ስቃይ፣ መንስዔው ኢትዮጵያ መሪ አልባ አገር በመሆኗ ነው። የደረሰው ሳይበቃ፣ በዚህ ምክንያትም ኢትዮጵያውያን ከደረሰብን መከራ ሳናገግም፣ ስቃዩ እና […]
↧
↧
“ጸርሁ በዓቢይ ቃል”
“ርኢኩ ታህተ ምስዋዕ ነፍሶሙ ለእለ ተቀትሉ በእንተ ቃለ እግዚአብሔር ወበእንተ ዘአቀቡ ህጎ። ወጸርሁ በቃል ዓቢይ ወይቤሉ እስከ ማእዜኑ እግዚኦ ቅድስ ወጻድቅ፤ ኢትትቤቀሎሙኑ ወኢትኴንኖሙኑ በእንተ ደምነ እምእለ ይነብሩ ዲበ ምድር” “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” እያሉ ከመሰዊያ በታች ሆነው የታረዱት ነፍሳት በታላቅ ድምጽ ሲጮኹ አየኌቸው (ራዕ 6፡9-10)። […]
↧
“ለመተማመን እንነጋገር”
በጀርመን የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ ሜይ 2 ቀን 2015 ዓመተ-ምህረት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በአካሄደ እለት እውቁ የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት አቀንቃኝና ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መስራችና መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና እውቁ የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝና አሰባሳቢ ማንነት በአንድነት መጽሀፍ ደራሲ አቶ የሱፍ ሃሰን በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። ስብሰባው በቅርብ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ባሰቃቂ ሁኔታ ለተሰዉት […]
↧
የመሪዎች እምባ
ከስም ልጀምር፣ የዛሬ ወጣቶች በተለይ ዘፋኞች ስማቸው በመጠኑ ተቆርጦ ወይም አንሶ ሲጠሩ እየሰማን ነው፤ ቴዎድሮስ – ቴዲ ብዙ ባያስከፋም ተያይዘው የቀጠሉት ዘፋኞች ግን እስከ አባታቸው ስለሚያሳንሱት ኢትጵያዊ ስም መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ የሆነብኝ ጊዜ አለ። እስቲ አሁን ጃህ ሉድ አጥሮ ነው ወይስ ተቆርጦ ቻቺ፣ ጃኪ፣ ጂጂ፣ አቢ፣ ኢሚ፣ ዮሲ፣ ጃኪ-ጎሲ፣ ሚሊ፣ ሚኪ፣ ዮኒ፣ … ልተዋቸው። እንደውነቱ […]
↧
↧
መሸነፍን በአሸናፊነት የተቀበሉ መሪዎች
በቅርቡ በሥልጣን ላይ እያሉ በምርጫ መሸነፋቸውን ባመኑበት ጊዜ ሥልጣናቸውን ያስረከቡት የናይጄሪያው ጉድላክ ዮናታን በአፍሪካ የ65 ዓመታት የምርጫ ዴሞክራሲ ጉዞ ከሚጠቀሱ ጥቂቶች መካከል አንዱ ሆነው ሰንብተዋል፡፡ ይህም ተግባራቸው በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ታላቅ ሥፍራ የሚሰጣቸው የፖለቲካ ሰው አድርጓቸዋል፡፡ በአፍሪካ በተካሄዱ በርካታ ምርጫዎች የሕዝብን ድምጽ በማክበር ሥልጣናቸውን ለተቀናቃኛቸው በማስረከብ የሕዝባቸውን ድምጽ ያከበሩ መሪዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ […]
↧
በአሜሪካ የንቦች ሞት ቁጥር ጨመረ
በአሜሪካ በብሔራዊ ደረጃ በተደረገ ምርምር የንቦች ቁጥር 40 በመቶ እንደሚቀንስ ተነገረ፡፡ ለንቦቹ መሞት ዋንኛ ምክንያት ንቦቹ በከፍተኛ ሃሳብና ጭንቀት ውስጥ መግባታቸው እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ሰኞ (ግንቦት 10/ሜይ 18) ዕለት የሜነሶታ የሕዝብ ሬዲዮ (Minnesota Public Radio News) እንደዘገበው በአሜሪካ ውስጥ በአጠቃላይ በተደረገው አዲስ ጥናት 6ሺህ ንብ አርቢዎች መጠይቅ የተደረገላቸው ሲሆን በዚህም መሠረት የሟች ንቦች ቁጥር በተለይ በበጋ […]
↧
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አምስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ብዙ ስለሰሩ መኮንን ሀብተወልድ መገለጽ አለበት ታሪካቸው የግድ ብዙዎችም አውቀው ይህን ተናግረዋል እየዘረዘሩ ታሪክ አስፍረዋል ቆፍጣናው […]
↧
ኢትዮጵያና አሜሪካ
ዱሮ ዱሮ ምዕራባውያን የሶቭየት ኅብረትን ኮሚዩኒዝም መስፋፋት ለመቋቋም ከእሥራኤል ሌላ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ አገሮችን ሲያስሱ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱርክና ፋርስ እየታጩ ነበር፤ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር የተወዳጀበትና በአስመራ ቃኘው ጣቢያን የተከለበት አንዱ ምክንያት ይኸው ነው፤ የፋርስ ጉዳይ ከንጉሠ ነገሥቱ መፈንቅለ መንግሥትና ሞት ጋር አበቃ፤ ቱርክ እያንገራገረም ቢሆን የሰሜን አትላንቲክ አገሮች ማኅበር ውስጥ አለበት፤ እሥራኤል በአረቦች አካል ላይ እሾህ […]
↧
↧
ሥልጣን ወደ ህወሃት?!
* “ግምገማ!” የኢህአዴግ ስድብ ሃይማኖት “ምግባረ ብልሹዎች ናችው፤ የሚታፈርባቸው ናቸው። እነሱን ብሆን ራሴን እንዳዋረድኩ ነው የምቆጥረው” ሲሉ የመድረክ ሊቀመንበር በየነ ጴጥሮስ ሃይለማርያምንና “ሌሎችም ቢሆኑ” ሲሉ የገለጹዋቸውን ባለሥልጣናት ምግባር ተቹ። ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ቢኖር ኢህአዴግ እንደሚሸነፍ ከ፱፭ በመቶ እርግጠኛ መሆናቸውንም አመለከቱ። ተቃዋሚዎችን ሕዝብን ወዳልተፈለግ አቅጣጫ እየመሩ ነው በማለት በመወንጀል የማስጠንቀቂያ መልእክት ያስተላለፉትን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ተከትሎ […]
↧
“እማይቻለው –ለተቻለው”
… እንዴት ነበር ከቶ ውጣ-ውረዱ…? …ተረተር፣ ሸለቆ…፣ አቀበት፣ ቁልቁለቱ…፣ …ጉድባው፣ ጉብታው…፣ አባጣ-ጎርባጣው…፣ …እሾኽ፣ እንቅፋቱ…፣ መሰናክል፣ ምቱ…፣ …ጠመዝማዛው ጉዞ…፣ እንዴት ነው መንገዱ? የያሬድ ልጅ ጠቢብ – መንፈስ የማኅሌታይ፣ የሰልስቱ ዜማ – ግዕዝ፣ እዝል፣ አራራይ፣ ነፍስን መሳጭ ቅኝት፣ ገነተ-ሕይወት አምሳል፣ አንቺሆዬ፣ ባቲ፣ ትዝታ፣ አምባሰል፣ ዓለም ኖታ ሳይነድፍ – የነበርንን እኛን፣ ሕዳሴ-ወጥበብ – ዳግም አስተዋውቀን፤ የ”ክፉ ቀን” ጓድህን፣ […]
↧
የምርጫና ነጻነት ቁልቁለት
* ከ45 ዓመት በፊት የፓርላማ ምርጫን ያሸነፉት አራት ሴቶች ሰማንያ አራት ዓመት ባስቆጠረው የኢትዮጵያ ፓርላማ የመጀመርያው ሕዝብ በቀጥታ የተሳተፈበትና እንደራሴዎቹን የመረጠበት ምርጫ የተካሄደው በ1948 ዓ.ም. ነበር፡፡ በቀዳሚው ምርጫ ካሸነፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንዷ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ናቸው፡፡ በታሪክ እንደተመዘገበው ወ/ሮ ስንዱ የመጀመሪያዋ የሴት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባልና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለአራት […]
↧
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፯
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፮” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ ስድስት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ መልስና አዲስ በታሪክ መዛግብት መጀመሪያ ምዕራፍ ስራ ታሪካቸው ምንም ሳይዛነፍ የተጻፈላቸው የሚነሱ ሁሌ እኚህ ስው ነበሩ […]
↧
↧
አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ . . .
የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ። “ሃሎ?” “ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?” “ነኝ፣ ምን ፈለግክ?” “ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።” “ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?” “99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!” “0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?” “አዎን […]
↧
የዛሬ 24 ዓመት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ባይቆጣጠር
ደርግ 17 ዓመታት ሙሉ በህወሓት እና ሻብያ የተከፈተውን ጦርነት ሲዋጋ እንደነበር እና ጦርነቱ በቀን ብቻ በሚልዮን የሚቆጠር ብር ያስወጣ ነበር። በመቶሺዎች የሚቆጠር ሰራዊት መግቦ፣ ታንክ እና ብረት ለበስ ተሽከርካሪ ነዳጅ እና ግዥ ፈፅሞ ማደር በራሱ ከፍተኛ ወጪ ነበር። ይህ ገንዘብ እንዳሁኑ የእርዳታ እና የብድር ገንዘብ ሳይሆን ህዝቡ ለእናት ሀገር እያለ ከሚያዋጣው እንደነበር ይታወቃል። በእርግጥ የሩስያ […]
↧
የኢሕአዴግ ቁልቁለት
“ፋክት” መፅሔት ላይ ቋሚ አምደኛ በመሆን በየሳምንቱ በወቅታዊ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን ወደ አንባቢ ሲያደርስ የነበረው ሙሉዓለም ገ/መድኅን አዲስ መጽሐፍ ለኅትመት አብቅቷል፡፡ የመፅሃፉ ርዕስ፡- የኢሕአዴግ ቁልቁለት ደራሲ ፡- ሙሉዓለም ገ/መድህን የገፅ ብዛት፡- 235 ዋጋ ለአገር ውስጥ፡- 52 ብር ለውጪ አገር፡- 20 ዶላር አጠቃላይ ይዘት መፅሃፉ በአራት ክፍሎች እና በአስራ አራት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፣ ክፍል […]
↧
ምርጫ ቢቀርስ?!
* “በየ5 ዓመቱ ምርጫ እያሉ ህዝብን ከማሰቃየት፣ እንደነ ሰሜን ኮርያ እና ቻይና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ነው ብሎ ማወጁ ይመረጣል” * “ኢህአዴግ ያሸነፈው ወደ ዘረፋ ስለገባ ነው እንጂ ተቃዋሚ ስለተዳከመ አይደለም” * ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ * ምርጫ ቦርድ የተቃዋሚዎች ውንጀላ መሰረተቢስ ነው ብሏል ባለፈው እሁድ በተከናወነው 5ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የተወዳደሩ ዋና ዋናዎቹ […]
↧
↧
የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ
የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 […]
↧
Ethiopian Election Results: Behind the Numbers
The truth may not be black or white. It may be gray. And embracing this fact is good for Ethiopia. Here is my take as an independent voice. My heart is for Ethiopia to find a bridge in reconciliation and mutual understanding. The Story of White The government is joyful that it had secured 100% […]
↧
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ “ሰላይ” ነው –ዲና ሙፍቲ
* “አቶ መለስ በጣም ይናፍቁናል” አሸባሪነት በኢትዮጵያ ሊስፋፋ ያልቻለው ሕዝቡ በሙሉ ሰላይ በመሆኑን ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡ ከአገር ተሰድደው የሚውጡት አብዛኛዎቹ ገጠሬ ወጣቶች እንደሆኑና ሟቹ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዳሴ አባት በጣም እንደሚናፍቋቸው ተናገሩ፡፡ ቀድሞ በቃል አቀባይነት ሲሰሩ የነበሩት በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኬኒያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ ስታንዳርድ ዲጂታል ከተባለ የኬኒያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ […]
↧