ታላቁ መጽሐፍ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ አስራ አራት በአንክሮ ሲነበብ «… የገዢዎች ቁጣ ሲነሳብህ ችግር እንዳትነቃነቅ ካለህበት አገር …» በሚለው የጸናህ የቆየህ በቃሉ ለካ! አንተ ኖረሃል ተሜ ባለውሉ በአንድ ብዕር ብቻ አላንዳች ፍራቻ ገዢን ያንበረከክ ዝምታን የሰበርክ ዕውነትን ያበሰርክ ተሜ ባለ ውሉ ተሜ ባለ ቃሉ ነጻነት ቃጭሉ የፍትህ አክሊሉ የታለ መሣሪያህ? የታለ ዝናርህ? የታለ ጦር ጋሻህ? [...]
↧