የመናገር፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ወዘተ መብቶች በሚከበሩባቸው አገራት በመጀመሪያ ደረጃ ፓርላማ የሚባል አካል ካላቸው ገዢው ፓርቲ የ99.6 በመቶ ወንበር አይዝም፤ በፓርላማው የተቀናቃኝ ፓርቲ አባልም አንድ ብቻ አይሆንም፡፡ ይህ ከሆነ ስብስቡ “ፓርላማ” ሳይሆን “የ… ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ” ነው የሚባለው፡፡ ከዚህ ሲያልፍ ረቂቅ ሕግጋትና ውሳኔዎች ሁሉ “በአክላሜሽን” ወይም በሙሉ ድምጽ ወይም “በእልልታ” አይደለም የሚጸድቁት፡፡ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላትም [...]
↧