የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ይሁን ባላንጣዎቻቸውን ወይም ከእርሳቸው የተለየ ሃሳብ የሚያመነጩትን “ስኳር ወዳድ”፣ “በስኳር የተታለለ”፣ … እያሉ ለእስር ሲዳርጉ የነበሩት አቶ መለስ፤ ሞት ሳይቀድማቸው በፊት ራሳቸው ያቋቋሙትና እርሳቸውን ደግሞ ደጋግሞ እያገላበጠ አንዴ ፕሬዚዳንት ሌላ ጊዜም ጠቅላይ እያደረገ ሲሾማቸው የኖረው “የምርጫ ቦርድ” ሕዝቡን በስኳር እየፈተነ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ “ስኳር” ቀምሰው ሳያውቁ ስለ ስኳር “አስከፊነት” ዘለግ ያለ መግለጫ በመስጠት ይታወቁ [...]
↧