ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጭት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን» እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ ማዕከል በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት [...]
↧