ብአዴን/ኢህአዴግ በምስራቅ ጎጃም ዞን “የምርጫ ግብረ ኃይል” በሚል አደረጃጀት የምርጫ ቦርድን ስራ እየሰራ መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ፀኃፊ አቶ ሳሙኤል አወቀ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የብአዴን ካድሬዎች በምስራቅ ጎጃም በተለይም ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ቤት ለቤት እየዞሩ ህዝቡ ካርድ እንዲያወጣ በሚቀሰቅሱበት ወቅት የምርጫ ካርድ አልወስድም የሚሉ ዜጎችን “አልወስድም ስትል ፈርም” እያሉ እያወከቡ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ [...]
↧