በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በአቶ ኦባንግ ሜቶ በተጠራው ስብስባ ላይ የመገኘት እድል አጋጥሞኝ ነበር:: በስብሰባው ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎችና ከአሜሪካ ግዛቶች የተሰባሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል:: የስብሰባው መሪ ሀሳብ “ስለ እያንዳንዳችን ከመናገር እያንዳንዳችን እንነጋገር” የሚል ድፍረትን፣ ግልፅነትን፣ መከባበርን፣ መነጋገር መቻልን ሃላፊነት በተሞላበት ስሜት ይቀርቡ በነበሩት አስተያየቶች የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ የተለየዩ የፖለቲካ አመለካከት፣ እምነት እንዲሁም የተለየዩ ብሄረሰቦች [...]
↧