ቀይ-ሽብር ሲጀምር ከደርግ ዲሞክራሲ ከወያኔ እኩልነት……ከሰማይ ዳቦ ስንጠብቅ ሰብዕናችን ተፍቆ ማንነታችን ተንቆ…..ከዕምነታችን ስንርቅ ውርደታችንን ተመልክተን፤ በቃ ማለት ካቃተን ታስሮ መታረድ አይቀርም እንደ በግ ተጎትተን —————– ዘመናት አስቆጥራ ብዙ ትውልድ ተሻግራ መቃብር ዛፍ ሲያበቅል፤ የብሶቱ ቀን ሲርቅ የደም አሻራ ሲጠፋ፤ የወላጅ እምባ ሲደርቅ ያኔ ይመስለኝ ነበር ታሪክ እራሷን የምትደግም ሕብረተ-ሰቡ ሲዘናጋ፤ ሰው ከሐዘኑ ሲያገግም [...]
↧