በዘመነ መሳፍንት ወቅት፤ ለስሙ በዙፋኑ ላይ የዘር ግንድ ያለውን ሰው አስቀምጠው፤ ራሳቸውን እንደራሴ በመሾም፤ ጉልበተኞች ያደረጉት ሁሉ ግልጽ ነው። የውጭ ሀገር መንግሥታት ደግሞ በወኪሎቻቸው አማካኝነት ፀረ-ኢትዮጵያ ሚና ተጫወቱ። በደንብ በዝርዝር የሚያስረዳ መዝገብ ግን አላገኘሁም። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሜ የተገነዘብኩትን ይዣለሁ። የእስክንድርያውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በመጠቀም፤ ግብፅና ቱርክ በአንድ በኩል፣ በፖርቹጋሎች የተጀመረውን ግንኙነት በመጠቀም፤ የካቶሊክ ቤተክርስትያን በሌላ በኩል፣ [...]
↧