አያቶቻችን የልጆቻችን መሬት ነች ብለው ደማቸውን አፍስሰው ሀገራችንን ከወራሪ ፋሽት ታደጉልን አባቶቻችን በውርስ እርስ በእርስ ሲጣሉ ሳይኖሩበት ሳያኖሩበት ይኸው አሉ ። ልጆች የሚሆነው ሳይገባቸው ውሉ የጠፋባቸውን አባቶቻቸው እያዩ ነው፤ ግራ መጋባታቸውን እየወረሱ ግራ እየተጋቡ ነው ፤ ወይ በሽሽት ላይ ናቸው፤ ነገር ግን እትብታቸው የተቀበረባትን ቀዬ ከማዶ ሆነው እያዪ የጨው አምድ ሆነው ቆመዋል፤ ብቻ ልቦቻቸው ያነባሉ። [...]
↧