ሀገር በብረት ሲታጠር — ‘ግንቦት ሃያህ’ ሲከበር፤ አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር — ዘመን በዘመን ሲቀየር፤ የስራ-ፈቶች ስብስብ መንጋ — ‘ፓርላማህ‘ሲከፈት ሲዘጋ..፤ ሱፍህን ገጥግጠህ — ከረባትህን ጠፍረህ፣ ወዝህን አሳምረህ — ካሜራ ፊት ቀርበህ፣ ጉሮሮህን..ጠርገህ — ፊትህ የከመርከውን ‘ሃያ ገጽ’ ገልብጠህ፣ ቁጥር እየቆጠርክ፣ አሃዝ እየጠራህ…፣ “ምናምን..ሺ.ቶን፣ ሚሊዮን ስልቻ፣ አምርተን አስገባን በዚህ ዓመት ብቻ…”፣ እያልክ ስትደሰኩር — ትንፋሽህ [...]
↧