ጠይም ፊትሽ መጥቆሩን፣ ትንፋሽሽ፣ ጥሎሽ መሸሹን፣ የፊትሽ ወዝ ማጠፈፉን አካል ቁመናሽ መርገፉን ሰማሁ እናቴ ሰማሁ፣ አይቻል የለ ችያለሁ። በዝምታ ተውበሽ በሰው ሸክም ተሞሽረሽ በኡኡታ … በዋይታ… መሸኘትሽን ሰማሁት አይቻል የለ ቻል አ’ረኩት የሆንሽውን ሳልጠይቅሽ ሳትነግሪኝ ጎንሽ ሆኜ ሳላዋይሽ ሳታዋይኝ ሞተሽ ቀብርሽ ሳልቆምልሽ ከቀረሁኝ እናቴ ሆይ! ፍረጂልኝ ፍረጂብኝ ምን ላድረገው? ምን ታረጊኝ? ስደት ዶጋ አመድ ያድርግህ! [...]
↧