. . . ነፍሱን አይማርና! ያ! ቀጣፊ ከንቱ – የሂትለሩ ጉብልስ፣ አሳልፎ ሄደ፤ መሰሪ ትምህርቱን – ለበረከትና…ለነ አቶ ሽመልስ፤ እነሱም በተራ፣ ለታችኛው አሽከር ነጭ ውሸቱን ዘርተው፣ አጨዱት. . .፣ ከመሩት. . .፣ ማተብ-አልባ አድርገው፤ ከወያኔ ካድሬ፣ የውሸት ፋብሪካ፣ ተመርታ የወጣች፣ የዘረኞች ቋንቋ፣ “ትግሬ ትጠላለህ” የሚሏት ቃል አለች፤ ያገር ወዳዶችን ተቃውሞ ማስቆሚያ፣ በይሉኝታ ገመድ ሸብቦ ማሰሪያ. [...]
↧