እንኳን ለ፪ሺ፯ ዓ.ም. አደረሠን፣ አደረሣችሁ! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፦ እኛ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ የመስከረምን ወር የመጀመሪያ ቀን የዘመን መለወጫ ዕለት አድርገን ማክበር የጀመርነው በሺህዎች ለሚቆጠሩ ዘመናት እንደሆነ ይታወቃል። በረዥሙ ታሪካችን እንደየአመጣጣቸው፦ ደስታን እና ሐዘንን፣ መከራን እና ብሥራትን፣ ጦርነትን እና ሰላምን፣ መቆርቆዝን እና መበልፀግን፣ ረሃብን እና አንፃራዊ ጥጋብን፣ ወዘተርፈ አስተናግደናል። ያለፈውን ዘመን ሸኝተን አዲስ ዓመት ስንቀበል ዘወትር መልካም [...]
↧