የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጥንታዊው የሼክ አህመድ ሳለህ አልዛህሪ (ሎምባርዲያ ሬስቶራንት የሚገኝበት) ሕንፃ ቅርስ መሆኑን በባለሙያዎች አረጋግጦ ክብካቤና ጥበቃ እንዲደረግለት ሲያሳስብ ቢቆይም፣ ሰሞኑን ባወጣው ሰርኩላር ሕንፃው ቅርስ አይደለም በማለት የቀድሞውን ውሳኔ ሽሯል፡፡ ቢሮው ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ለአዲስ አበባና ዙርያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ጽፎ በነበረው [...]
↧