የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ “በድርብ አኻዝ አድጓል፤ እያደገም ይሄዳል፣ ይቀጥላል፣ ይመነደጋል” እየተባለ “በተዘመረበት” ዓመታት ሁሉ በአንጻሩ በገሃድ ያለውን እውነታ ቁልጭ ባለ መልኩ የሚያሳዩ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል፤ እየወጡም ይገኛል፡፡ ሆኖም እነዚህ ዘገባዎች በሥልጣን ላይ ያሉትን ሁለቴ እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው እንደሚገባ ቢነገርም ምላሹ የተለመደው “የልማት ጸሮች” ያወጡት፣ “የአሸባሪዎች እጅ ያለበት”፣ “የኒዎ-ሊበራል አቀንቃኞች ዘገባ”፣ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምኞት”፣ ወዘተ ከሚል አልፎ አያውቅም። [...]
↧