የሀገር ውስጥ ምሁራን በፊደሎቻችን ላይ ብዙ ዓይነት ቅሬታዎችንና ጥያቄዎችን ሲያነሡ ቆይተዋል አሁንም በየ ብዙኃን መገናኛው ማለትም በየነጋሪተ ወጉ(Radio) በየ ምርአየኩነቱ (Television) እና በየ መጣጥፉ በማንሣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለውጦችንም ማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም እንዲመቻቸው ይመስላል የፊደሎቻችን ባለቤት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሆኑን ልቦናቸው እያወቀ እንደፈለጉ ያለከልካይ እና ጠያቂ ለውጥ ለማድረግ እንዲመቻቸው ከፊደላቱ ባለቤት ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተቃውሞ እንዳይነሣባቸው የፊደላቱን ባለቤት [...]
↧