በአሁኑ ሰዓት በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያዊ የዜና መለዋወጫ መስኮች፤ “ትግሬዎች በዚህ መንግሥት ተጠቅመዋል? ወይንስ አልተጠቀሙም?” የሚለው ጉዳይ ዓይነታ መወያያ ሆኖ፤ መድረኮቹን ሁሉ አጣቦ ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ፤ አንድን ጉዳይ ኢትዮጵያዊ ታጋዮች ሲያነሱ፤ ከትግሉ ዋና ግብ አንጻር ነው። እንዲያው ለወግ ያህል ወይንም ቁጭትን ለመዘርገፍ የሚደረግ ውይይት፤ የታጋዮችን ቀልብ አይስብም። ይኼ ጉዳይ በትግሉ ሂደት ውስጥ ለኢትዮጵያዊ ታጋዮች ምን ይጠቅማል? ትግሉን [...]
↧