መንግስታት በተለያየ መልኩ ትርጉመው ያቀረቡትን ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ህግ ያወጣሉ፡፡ በእርግጥ በአዲስ መልክ በሽብር ላይ የታወጀው ዘመቻ በአሜሪካ ግፊት የመጣ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2001 አሜሪካ ከደረሰባት የሽብር ጥቃት በኋላ “war on terror” እንዲሁም “counter terrorism” የተሰኙ ዘመቻዎችን ነድፋ ተንቀሳቅሳለች፡፡ አሜሪካ ወዳጅም ሆነ የቀዩ ባላንጣዎቿን ሳይቀር ደልላም ሆነ ተማጽና የጀመረችው ይህ “ጸረ ሽብር ዘመቻ” መንግስታት በየ አገራቸው [...]
↧