መግቢያ በዚህ ጽሁፍ ሥር ለውይይት ይሆን ዘንድ የምናነሳው ኣሳብ constitutional patriotism ወይም ህገ መንግስታዊ ቀናዒነት ወይም ኣርበኝነት የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ባለፈው በተከታታይ ካቀረብኳት የConventional Cultural Unity ወይም በስምምነት ላይ የተመሰረት ባህላዊ ውህደት ካልኩት ኣሳብ ጋር እንዴት እንደሚለያይና በኢትዮጵያ ሁኔታ ከሁለቱ ኣሳቦች የትኛው ተገቢና ችግር ፈቺ ሊሆን እንደሚችል ኣሳብ ለማፍራት ነው። በቅድሚያ ኣንድን ፖለቲካዊ የሆነ ፍልስፍና [...]
↧