ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት በቅድሚያ ሀገር ማለት ራሱ ምን ማለት ነው? እንዴትስ ትፈጠራለች? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይኖርብናል፡፡ ሀገር ማለት በአንድ ጥላ ስር የሚኖርባት ትልቅ ቤት ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ጋርዮሽ ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ከመንደር ከቀየ የገዘፈች የጋራ ጥቅም የፈጠሩ ሕዝቦች የራሳችን የግላችን የሚሉት የተከለለ ምድርና በውስጡ ያሉ ሁሉ ነገሮች ማለት ናት፡፡ ሀገር እንዴት ትፈጠራለች? [...]
↧