እኔ ልሙት አንቺ፣ አንቺ ትሞች እኔ፣ ሳያውቅብን ቀኑ፣ ሳናውቅበት ቀኑን፣ በቁም ያለን መስሎን፣ እናቴ እኔና አንቺ፣ ተለያይተን ቀረን። ሞትን መቀበር ነው፣ በጉድጓድ መከተት፣ ከምድር በታች መዋል፣ ብለህ አትናገር፣ ሌላ ሞትም አለ፣ አታውራ ዝም በል። በእኔና በእናቴ፣ በልጅና በእናት፣ ደርሷል ቆሞ መሞት፣ ቀኑ ወር ተክቷል፣ ወራት ብዙ ዓመታት፣ ሳታየኝ ሳላያት። አዎን! አለች አለሁ፣ አለን እንላለን፣ በስጋ [...]
↧