ወንድ ልጅ ሲወለድ አባት ለተወለደው ልጁ ጠብ – መንጃ (ጠመንጃ) ለመግዛት ደፋ ቀና ከሚባልበት አካባቢ ነው ተወልጄ ያደኩት፡፡ ይህ የሚደረገው ደግሞ በቂ ሃብት ስላለ ሳይሆን “ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንደ አባቱ እንዝርት አቅርቡለት ይፍተል እንደ እናቱ” የሚለው የንቀት አባባል በልጁ ላይ ሲያድግ እንዳይደርስበት ከወዲሁ ለማዘጋጀት ነው፡፡ እንዲያውም ልጅ በልጅ ተሸንፎና ተመትቶ እያለቀሰ ወደ ወላጆቹ ለእርዳታ [...]
↧