ከላይ የጠየቅነው ጥያቄ ዛሬ የተነሳ አዲስ ነገር አይደለም። ኢህአዴግ መሰረቱን ዝርፊያ ላይ ያደረገ አገር አስተዳዳሪ መሆኑ ግብሩ ራሱ ምስክር ነውና “ሌባ አገር አስተዳዳሪ” ስለመሆኑ ማስተባበያ ሊያቀርብም አይቻለውም፤ አያስፈልገውም። ሌብነቱ አገርንና ህዝብን ወደ ገደል እየሰደደ መሆኑ ግን ሁሌም የሚያስጨንቅ ነውና ዛሬ እንደ አዲስ አነሳነው እንጂ!! ኢህአዴግ ግዙፍ፣ ሃብቱ በዶላር ካልሆነ በብር የማይቆጠር፣ በህገወጥ ንግድ ሰላማዊ ነጋዴዎችን [...]
↧