በመጪው ምርጫ የግብጽ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ የሚባሉት የግብጽ ጦር ዋና አዛዥ ፊልድ ማርሻል አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ከሩሲያ ጋር የ2ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ ውል ድርድር ላይ መሆናቸው በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ረቡዕ ሞስኮ የገቡት አል-ሲሲ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር የመሣሪ ውሉን በተመለከተ የሁለት ለሁለት ውይይት እያደረጉ ናቸው፡፡ ከግብጽና ከሩሲያ በኩል የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ሚኒስትሮች የድርድር ውሉ ዋና አካላት [...]
↧