የግብፅ መንግሥት በታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ በተመለከተ ሱዳን ለኢትዮጵያ የሰጠችውን ድጋፍ ለማጨናገፍ፣ ሱዳንን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ መጀመርዋን ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ የተለያዩ የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ሰሞኑን እንደዘገቡት፣ የግብፅ መንግሥት የተለያዩ የመንግሥት አመራሮችና ፖለቲከኞች ከሱዳን መንግሥት አቻዎቻቸው ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጀምረዋል፡፡ ለአብነት ከተጠቀሱት መካከል የግብፅ አል ዋፍድ ፓርቲ ሊቀመንበር ሳይድ አል ባዳዊ በካይሮ ከሱዳን አምባሳደር ከማል [...]
↧